አገራችን ከተቀበለቻቸውና ካፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መካከል ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት ግምባታ ፕሮግራም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት በሀገራችን የካርበን ልቀትን ለመቀነስ ከተመረጡት አራት ምሰሶዎች አንዱ የደን ሀብት ዘርፍ ነው፡፡ ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ ዘርፍ በአለፉት ዓመታት በክልላችንም ሆነ በአገራችን ደረጃ በርካታ የደን ጥበቃ፣ ልማት፣ አጠቃቀምና ቁጥጥር ሥራዎች በግብርና ቢሮ እና በሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑት ድርጅቶች የተሰሩ ቢሆንም የተፈለገውን ያህል ውጤት አላስገኘም፡፡

የክልሉ የተፈጥሮ የደን ሀብት ባለው የእንስሳት ሀብት ጫና፤ የእርሻ መሬት መስፋፋትና  ዘላቂነት በሌለው የደን ሀብት ውጤቶች አጠቃቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ የደን ሀብቱ እየሳሳና እየጠፋ በመምጣቱ ለአፈር መሸርሸርና ለምነት መቀነስ ጋር ተያይዞ ለምርትና ምርታማነት መቀነስ እንዲሁም ለውሃ አካላት ጥራትና መጠን መቀነስ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡

በአሁኑ ወቅት በክልሉ የተሻለ የተፈጥሮ ደን ሀብት የሚገኝባቸው ቆላማው ምዕራባዊ አካባቢዎች ሰሜን ጎንደር፣ አዊ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ሲሆኑ በእነዚህ አካባቢዎች ያሉት ቁጥቋጦዎች (Bush, woodlands) እና ሌሎች የውሃ ዳርቻ ደኖችን ጨምሮ ሽፋኑ 1,651,370 ሄ/ር ሲሆን በከፍተኛ ቦታዎች በተፈጥሮ ጥቅጥቅ ያለ ደን 463,950 ሄ/ር ይደርሳል፡፡ በሰው ሰራሽ ደን አነስተኛ ስፋት ያላቸውን የግል ደንን ሳይጨምር ሽፋኑ 62,970 ሄ/ር ሲሆን ይህም በክልሉ ውስጥ በ1,538 ማህበራት ይዞታ ስር እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአጠቃላይ ክልሉ ካለው የቆዳ ስፋት 2,178,300 ሄ/ር (13.85%) በተለያዩ የደን ዓይነቶች የተሸፈነ እንደሆነ ከግብርና ቢሮ የተገኙ መረጃዎች (BOA/CIFOR, 2015) ይጠቁማሉ፡፡

በሌላ በኩል ቡድኑ የመስክ ቅኝት ባካሄደባቸው አካባቢዎች አርሶ አደሩ ያለውን የእርሻ መሬት ወደ ደን ልማት በመለወጥ የግል ደን ይዞታን ከማስፋፋት አንፃር በአንዳንድ ወረዳዎች ከፍተኛ የደን ሽፋን እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡ ለአብነት ያክል ከፍተኛ የደን ሽፋን ያላቸው ወረዳዎች ፋግታ ለኮማ 31.63% እና ባንጃ 37.65% ሲሆኑ በአንፃራዊነት ዝቅተኛ የደን ሽፋን ያላቸው ወረዳዎች ሜጫ 14.5% እና ዳንግላ ወረዳ 15% ናቸው፡፡ በሌላ በኩል በቆላማው አካባቢ ጃዊ ያለው የተፈጥሮ ደን ሽፋን 49.13% እንደሆነ ከአዊ ዞንና ከወረዳዎች የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የክልሉን የደን ሀብት ይበልጥ ለማስፋፋት፤ እሴት ጨማሪ ለማድረግና በደን ውጤቶች አቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ነባር የመንግስት ደኖችን ተረክቦ ደን በማልማትና የተለያዩ የደን ምርት ውጤቶችን ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ኢንተርፕራይዙ ከ2002 እስከ 2008 ዓ.ም ባካሄዳቸው የስራ እንቅስቃሴዎች በክልሉ ውስጥ 89,466 ሄ/ር ከመንግስት ደን ተረክቦ ወደ 57.37 ሚሊዮን ችግኝ አፍልቶ 22 ሚሊዮን ችግኝ በተመረጠው 8,920 ሄ/ር ተካላ እንዳካሄደና ከተተከለው ከ66.7% እንደጸደቀ ሪፖርቱ ያሳያል (ሚያዝያ 2008 ዓ.ም የተዘጋጀው ልሳነ አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የወጣው መጽሄት እና የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ግንቦት 2008)፡፡ በተጨማሪም የደን ሀብት እያስገኘ ያለው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ጠቀሜታዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

ሀ/ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው፡- አንዳንድ ባለሀብቶችም ሆኑ ግለሰቦች በክልሉ ያለውን የደን ሀብት ውጤቶችን ወደ ውጪ አገር በመላክና በአገር ውስጥ በማዘዋወር ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በማዋል ላይ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅ/ጽቤት ባህር ዳር በተገኘው መረጃ የአጠና ምርት በግለሰቦች ወደ ውጪ አገር የተÕÕዘው በ2006 ዓ.ም 46,327 ሜ/ኩ፣ በ2007 ዓ.ም 60,805 ሜ/ኩ፣ በ2008 ዓ.ም 24,911 ሜ/ኩ በድምሩ 132,043 ሜ/ኩ ወደ ውጪ አገር የተÕÕዘ ሲሆን ከዚህ የደን ውጤት የተገኘ ገቢ በ2006 ዓ.ም ዋጋ በዶላር 2,020.024፣ በ2007 ዓ.ም ዋጋ በዶላር 2,278,407፣ በ2008 ዓ.ም ዋጋ በዶላር 1,058,764 በድምሩ 5,357,195 ዶላር ክልሉ ለአገሪ~ የውጪ ምንዛሬ በማስገኘት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዳደረገ ማስረጃው ይጠቁማል፡፡

በሌላ በኩል በአገር ውስጥ ለማገዶና ኮንስትራክሽን፣ ለቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ፤ ለከሰል ምርት ወዘተ አገልግሎት ለማዋል በግለሰቦችና በማህበራት ከሚመረተው ውጪ የአማራ ደን ኢንተር ፕራይዝ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ውስጥ ከ1,807.8 ሄ/ር ደን ላይ 431,000 ሜ/ኩ የደን ምርት ውጤቶችን አምርቶ ለገቢያ አቅርቧል፡፡

በክልሉ ውስጥ የደን ሀብቱን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲዘዋወር በ2008 ዓ.ም ከልማት ክፍያው (ሮያሊቲ ፊ) የተገኘው ገቢ 19.091 ሚሊየን ብር ሲሆን ከፍተኛ ገቢ የተሰበሰበበት አዊ ዞን 12.5 ሚሊየን ብር እንደሆነ ከግብርና ቢሮ የተገኘው ማስረጃ ያስረዳል፡፡ የጥናት ቡድኑ በመስክ በየወረዳዎች ተዘዋውሮ ባገኘው መረጃ የአጠና እና የከሰል የደን ምርት ውጤቶች ሲዘዋወሩ ከልማት ክፍያ የፋግታ ለኮማ ወረዳ በ2008 ዓ.ም የተገኘው ብር 9.4 ሚሊዮን ሲሆን ከሜጫ ወረዳ ደግሞ የተገኘው ብር 1.73 ሚሊዮን መሆኑን ከወረዳዎች የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ በቆላማው አካባቢ በተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከተፈጥሮ የደን ሀብት እየተመረተ ያለው የተፈጥሮ ዕጣንና ሙጫ ለአገር ውስጥና ለውጪ ገቢያ እየቀረበ የውጭ ምንዛሬበማስገኘት ላይ ነው፡፡ በአጠቃላይ የደን ውጤቶች ለአገሪቱም ሆነ ለክልሉ ህዝብ ለተለያዩ አገልግለቶች ጥቅም ከመዋሉ በተጨማሪ ለአገሪ~ የውጪ ምንዛሬ በማስገኘት ለኢኮኖሚው ዕድገት እያደረገ ያለው አስተዋኦ ከፍተኛ ነው፡፡

ለ/ ማህበራዊ አገልግሎት፡- ማህበረሰቡ የደን ሀብቶችን ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግለቶች ማለትም ለመድሃኒት፣ ለስብሰባ ቦታ፣ በጸሐይና በዝናብ ጊዜ ለመጠለያነት፤ ለአምልኮት ወዘተ እንዲሁም የደን ውጤቶችን ለሀይል ምንጭነት፣ ለቤትና ለእርሻ መሳሪያነት፣ ወዘተ አገልግለቶች ይጠቀሙበታል፡፡

ሐ/ለአካባቢ ደህንነት ያለው አስተዋጽኦ፡- የደን ሀብት በየአካባቢው ለሚገኙ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ሀብቶች ደህንነት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በተራራማ ቦታዎች የአፈር መሸርሸርን በመቀነስና ለምነትን እንዲጨምር በማድረግ፤ በክረምት ወቅት ከተራራማ አካባቢዎች የሚነሳው የዝናብ ጎርፍ በታችኛው የተፋሰስ ክፍል በሚገኙት አካባቢዎች ላይ የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት በመከላከል፤ የተጎዱ አካባቢዎች የማምረት እቅማቸው እንዲጎለብት በማድረግ፤ የውሀ ሀብት በመጠንና በጥራት በማሻሻል፤ ለዱር እንስሳት ለመጠለያነት አገልግሎት በመስጠት የመሳሰሉትን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ በተለይ ደግም በአሁኑ ወቅት የዓለም ችግር የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ዓለም አቀፍ ትኩረት ተሰጥቶት በአገራችን ለተቀረጸው የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንÕዴ ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጅ ውስጥ የካርበን ልቀትን በመቀነስ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ነው፡፡

በመሆኑም የደን ሀብት ለኢኮኖሚው፣ ለማህበራዊና ለአካባቢ ደህንነት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ መንግስትም ሆነ ህዝብ ለደን ልማቱና ጥበቃው ትኩረት በመስጠት ሀገሪቱ በደን ልማት ያላትን ሁለንተናዊ አቅም መጠቀም ይኖርባታል፡፡

በዚሁ መነሻ የደን ሀብቱን ይበልጥ ለማጠናከር የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 232/2008 ተቋቁሞ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ከአካባቢ ጥበቃ፣ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ፤ የደን ጉዳዮች ከግብርና ቢሮ እንዲሁም የዱር እንስሳትና ፓርኮች ልማት ጉዳዮች ከባህል፣ ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ ተመሳሳይ ተግባራትን በአንድ ላይ በማደራጀት ውጤታማ ሰራዎችን ለማከናወን በዝግጅት ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ባለስልጣኑ የመስሪያ ቤቱን ዓላማዎች መሰረት ያደረገ የአገልግሎት አሰጣጥ በጊዜ፣ በመጠን፣ በወጪና በጥራት የሚለካ፤ የደንበኛውን ፍላጐት ሙሉ በሙሉ የሚያረካ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ የአሠራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የአሰራር ማሻሻያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡

ቀደም ሲል በሶስት መ/ቤቶች ተግባር ላይ ውለው ከነበሩት አደረጃጀቶች ውስጥ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማት የስራ ሂደት የደን ጥበቃና ልማት ጉዳይን፤ የአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነትን ማረጋገጥ ዋና የሥራ ሂደትን እንዲሁም የዱር እንስሳት ጥናት፣ ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ዋና የስራ ሂደትን ለመፈጸም የተቀረጹ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናቶችን መነሻ አድርጎ በመውሰድ በአዲስ መልክ ከተዋቀረው የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ተግባርና ሀላፊነት ጋር እንዲጣጣሙ ለማድረግ ይህ የአሰራር ማሻሻያ (BPI) ተዘጋጅቷል፡፡

የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በክልል፣ በዞን፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የተዋቀረ ሲሆን በክልል ደረጃ አምስት ዋና የስራ ሂደቶች ማለትም፡-

ü  የአካባቢ ጥበቃ ዳይሬክቶሬት

ü  የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት

ü  የህብረተሰብ ግንዛቤና የመረጃ ተደራሽነት ዳይሬክቶሬት

ü  የአካባቢ ሁኔታና ለዉጥ ዘገባ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት

ü  የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት

በዚህ መሰረት ከተደራጁት የስራ ሂደቶች መካከል አንዱ ለሆነው የደን ጥበቃ፣ ልማትና አጠቃቀም ዋና የስራ ሂደት የመሰረታዊ የስራ ሂደት ማሻሻያ ጥናት ተካሂዷል። በተሻሻለው የስራ ሂደት የደን ልማት፣ የደን ጥበቃ፣ የደን አጠቃቀም፣ የደን  ቁጥጥር፣ የደን ማኔጅመንት ፕላን ዝግጅት፣ የህግ ማዕቀፍ ዝግጅት፣ ፕሮጀክት ቀረጻ፣ ሀብት ማፈላለግና ትግበራ፣ ስልጠና፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ዋና ዋና ተግባራት ናቸው። 

Online Users

We have 3 guests online
About Service Delivery