ዜና አብክመ አካባቢ ጥበቃ /ሃምሌ 17/2011ዓም /

ፓርካችን የሁላችን በሚል መሪ ቃል በስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ክልል አቀፍ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ተካሄደ

የአማራ ክልል ወጣቶች አደረጃጀት ከሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደርና ከስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ጋር በመተባበር ሃምሌ 15/ ቀን 2011ዓም በስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ሳንቃ በር ተብሎ በሚጠራው አከካባቢ ክልል አቀፍ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

በችግኝ ተከላ ዘመቻው ከፌደራል እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ ያሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የሁሉም ዞኖች ወጣቶች አደረጃጀት አመራርና አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ፕሮግራም ላይ የተገኙት የዞን የክልልና የፌደራል አመራሮች ችግኙን ከመትከል ባለፈ በየጊዜው መንከባከብ እንደሚገባ በተከላው ለተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዚህ የተከላ ቀን ከ35000 በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ከ3284 ተሳታፊዎች መሳተፋቸውንም ከስሜን ተራሮች ብራዊ ፓርክ ያገኘንው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የአለም አካባቢ ቀን ተከበረ

 

በየዓመቱ ግንቦት 28 ቀን የሚከበረው የአለም አካባቢ ቀን በአለም ለ44ኛ፤ በአገር አቀፍ ለ24ኛ እና በክልል ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ ተከበረ፡፡ በዚህ አመት አገር አቀፉ የአለም አካባቢ ቀን በአማራ ብሄራዊ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በመቅደላ ወረዳ በደማቅ ስነስርአት የተከበረ ሲሆን በአሉም ክቡር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒሰቴር ሚንስትር ዶ/ር ገመዶ ዳሌና ሌሎች ከፍተኛ የክልልና የፌደራል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በደማቅ ስነ ስርአት የተከበረ ሲሆን መሪ ቃሉም ሰዉንና ተፈጥሮን እናስተሳስር የሚል ነበር፡፡ በአሉም በመስክ ጉብኝትና በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡ በበአሉም ላይ ልዩ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች የማበረታቻ ሽልማትና ስጦታ ተሰጥቷል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ክልላዊ የአካባቢ ቀን ደግሞ የሰውና ተፈጥሮ መስተጋብር ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ቃል በደቡብ ጎንደር ዞን በጉና ተራራ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ ላይ ተከብሯል፡፡ በአሉም የጉናን ተራራና ተፋሰሶች በመጎብኘት የተከበረ ሲሆን በደብረታቦር ከተማም በአሉን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተደርጓል፡፡ በአሉን አስመልክቶ የክልሉ የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በላይነህ አየለ እንደገለጹት ይህንን በአል ስናከብር እያንዳንዳችን የሚጠበቅብንን የአካባቢ ጥበቃ ተግባር ለመፈጸም ቃል በመግባትና ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት ሊሆን እንደሚገባ በመግለጽና ለበዓሉ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉትን የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅትንና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲን አመስግነዋል፡፡ በአሉም ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ከጉና አዋሳኝ ወረዳዎች በመጡ ተሳታፊዎች በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል::

Online Users

We have 4 guests online
About Service Delivery